በታሪክ እንዳየነው የኦሮሞ የነፃነት ትግል ማሸነፍ ያቃተው የውጭ ጠላት ይልቅ ከራሱ የበቀሉት ከሃዲዎችን ነው!!

[ፈይሶ ከድር]

ዛሬ በአቢይ አህመድ፣ ፊት አውራሪነት፣ በ ታዬ ደንደኣ፣ ግራ አዝማችነትና በሽመልስ አብዲሳ፣ ቀኝ አዝማችነት የኦሮሞ ህዝብን ዳግም በማሞኘት ለህዝቡ መብት፣ ማንነትና አንድነት ለማምከን የሚደረገውን እንቅስቀሴ የዳግም ውርደት ደውል መሆኑን የኦሮሞ ሕዝብ የግድ ማወቅ ያለበት እውነታ ነው። የሚገርመው ደግሞ እነዚህ የጥፋት ሃይልች የኦሮሞ ህዝብ ምንም አያውቀንም ብለው በማሰብ ለኦሮሞ ህዝብ መብትና ነፃነት የሚቆሙ መስለው በማምታታት በኦሮሞ ስም ስልጣን መያዛቸው ደግሞ ግልጽ ነው።
.
ሞኝ በእባብ ሁለቴ ይነድፋል የሚባለው የኦሮሞ ህዝብ እነ ጎበና የነፍጠኛው ስርዓት ተላላኪ ሆነው በ20ኛው ክ/ዘመን የኦሮሞ መንግስታትን ማፈራረሳቸው፣ የኦሮሞ እናቶችን ጡት ማስቆረጣቸው፣ በጨለንቆ ጦርነት ወደ 30ሺ ኦሮሞዎች ያለቁበትን የብሄሩን ማንነት በማዋረዳቸው መብቱ መረገጥና ህዝቡ በማንነት፣ በባህሉና በታሪክ እንደቆሻሻና በሀገሩ እንደ ዜጋ እንዳታይ ማድረጉ መቼም መዘንጋት የለበትም። ስለዚህ አሁን በኦሮሞ ህዝብ ላይ ዳግም እንደማይደርስ ግን እነዚህ የነፍጠኛው ቅሪት ርዝራዦችና ተላላኪዎቻቸው የጥፋት መልዕክት ሕዝባችን በጥብቅ መገንዘብ አለበት።
.
የብልጽግና ምኞት የኦሮሞን ህዝብ በተለያዩ ቦታዎች ከፋፍሎ አንድነቱን መዳከም። ኦሮሚያን ካርታ በመቆራረጥ የኦሮሞን ህዝብ አንድነት በማሳጣት ከፋፍለው ለመግዛት ቆርጠው መነሳታቸውን በተደጋጋሚ አውጀዋል። የጥፋት ውሃ ያገኘውን ሁለ አይምርም እንደሚባለው የብልጽግና ፓርቲ የፊውዳሉን ከፋፍለህ ግዛ ስርዓት ለመመለስ ታላቁን የኦሮሞ ብሄር ራሱን በራሱ የማስተዳደርና የራሱን ውሳኔ በራሱ የሚወስንበትን የኦሮሚያ ክልልን ለማፍረስና ለመበታተን የሚያስችላቸውን ስትራቴጂ ነድፈው መንቀሳቀስ ከጀመሩ ቆይተዋል።
.
የብልጽግና ስትራቴጂ የኦሮሞ ህዝብ ለመብቱ በአንድነት እንዳይቆምና እንዳይታገል የአንድነት ድምፁን ለማሳጣት፣ በሀገሪቷ የፖለቲካው መስክ ሕዝቡ ያለውን የወሳኝነት ሚና ለማምከን የተቃጣ በመሆኑ የኦሮሞ ህዝብ ይህንን አስተሳሰብ በአንድነት በመነሳት ማምከን አለበት። በሌላ አነጋገር የብልጽግና ስትራቴጂ በኦሮሚያና በኦሮሞ ህዝብ ብቻ ላይ የተቃጣ የጥፋት መልዕክት ድምፅ መሆኑን ተረድቶ መላው የኦሮሞ ህዝብ የሉአላዊነታቸው መግለጫ በሆነው ህገመንግስታዊ ስርዓት መሰረት መብቱን ማስከበር አለበት።
.
የብልጽግና ፓርቲና ሌሎች የፊውዳል ቅሪቶች አስተሳሰብ የያዙ ፓርቲዎች እያስተጋቡ ያሉት የጥፋት ፕሮፖጋንዳ በኦሮሚያ አንድነትና በማንነቱ ላይ የተቃጣ በ21ኛ ክ/ዘመን የነፍጠኛን ስርዓት በአዲስ መልክ ለመመለስ ትምክተኞችና
ጠባቦች የሚያሰሙት ድምፅ በመሆኑ የኦሮሞ ወጣቶችና ሊሂቃን/ ምሁራን የኦሮሞን ህዝብ አንገት ስያስደፋ የኖረውና በህዝብ ልጆች እልህ አስጨራሽ ትግል የወደቀውን ስርዓት ግብዓተ መሬት በእውን እንዳልተረጋገጠ መሳያ በመሆኑ ይህንን የነሱን አስተሳሰብ ለማምከን መላው የኦሮሞ ሕዝብ በአንድነት ቆመው የግድ መፋለም አለበት።
.
የትምክተኛው ሀይል የአሮሞን ህዝብ ታሪክ ከመካዳቸውም በተጨማሪ የኦሮሞን ህዝብ የበታች አድርጎ ራሱን የኢትዮጵያ የበላይ ጠባቂ ሆኖ መታየት ይፈልጋል። ኢትዮጵያ እንደሀገር ከተመሰረተች ግዜ ጀምሮ የኦሮሞ ህዝብ እየተጫወተ ያለውን የማይተካና የወሳኝነት ሚና ትምክተኞችና ጠባቦች በየትኛውም ሳይንሳዊ ትንታኔ ማሳመን አይቻልም። የኦሮሞ ህዝብ ታሪኩ በነገስታት በመዋላ ዜና ፀሃፍትና የኢትዮጵያ ታሪክ አዋቂ ነን የሚሉ የልምድ ፀሃፊዎች በትክክል ባይፅፉም የኦሮሞ ህዝብ ትክክለኛ ታሪከ ግን ለኢትዮጵያ መመስረት፣ አንድነትና እድገት የማይተካ አስተዋፅኦ ማበርከቱነ ነው። ትምክተኞች ግን የኢትዮጵያ ጠባቂ ሆነው በግብዝነት ለመታየት ስለሚፈልጉ ይህንን ግልፅ ሀቅ አይቀበሉትም።
.
ኦሮሞን ብሄርን በመከፋፈል አንድነቱን ለማምከንና ማንነቱን ለማዋረድ ከተሰለፉት የድሮው የነፍጠኛ ርዝራዦች ጋር አጃቢ ሆነው ዛሬ የተሰለፈው የብልጽግና ፓርቲ ተብዬው አታላይ የነፍጠኛውን ፈላጎት ለማስፈፀም የተሰበሰቡትና የተደራጁ መሆናቸው መታወቅ አለበት። እነዚህ በብልጽግና ውስጥ ያሉት ኦሮሞ ተብዬዎች በነፍጠኛው ስርዓት ያገለገሉ ከመሆናቸውም በላይ የኦሮሞን አንድነት ከማይወዱት ጋርም በማይታወቅና ተጨባጭ ባልሆኑ አጀንዳዎች ዙሪያ የውሸት አንድነት የመፍጠራቸውም ሁኔታ ይህንኑ ያረጋግጣል። ይህ የሚያሳየው እነ ኦፌዳንና አህኮ የኦሮሞ ህዝብ በነፍጠኛው ስርዓት የተነጠቀ በትግሉ አሁን የተጎናፀፈውን መብቶችንና ያረጋገጠውን ተጠቃሚነት ለመቀልበስ ከሚታገለት ጋር መሰለፋቸውን ነው።
.
የብልጽግና ፓርቲን ወክለው የሚንቀሳቀሱ ከኦሮሞ ወጥቶ ነገር ግን የነፍጠኛ ተላላኪ የሆኑት አሮሞ ተብዬዎች እና የነፍጠኛ ስርዓት ናፋቂዎች ሕዝባችን በአንድነት ቆሞ ከላስወገዳቸው የተደገሰልን የጥፋት ድግስ እጂግ በጣም ከባድ ነው። ስልጣን ከያዙ በኋላ ግን የህዝቡን መብትና አንድነት ለማምከን የተሰለፉ መሆናቸው ከሚናገሩትና የተሰበሰቡበት ስብስብ በግልፅ ያሳያል። ዋነኛው አፍቃሬ ነፍጠኛ ወደ ሆነውን አንድነትን መቀላቀላቸው ይህንኑ ያረጋግጣል። ጉዳዩ ጅብ በማያውቁት ሀገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ ይላል እንደሚባለው ነውና ማን ከማን ለምን እንደሰለፈ ኦሮማዊያን ጠንቅቀው ያውቃሉ የሚል እምነት አለኝ።

ቸር እንስንብት

Advertisement
%d bloggers like this: