የኢሬቻ በዓል በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች በዱባይ ከተማ በድምቀት ተከበረ፣

የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል “ኢሬቻ ለሀገር ማንሠራራት” በሚል መሪ ሃሳብ በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ዱባይ ከተማ በድምቀት ተከበረ፡፡

መርሃ -ግብሩ በአባ ገዳዎች እና ሃዳ-ሲንቄዎች መሪነት በፓርኩ ውስጥ በተዘጋጀው ቦታ ‘’በኢሬፋና’’ ሥነ-ሥርዓት ወይም ባህላዊ ምርቃት ተጀምሯል፡፡

በበዓሉ ላይ በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት ተጠባባቂ ጉዳይ ፈጻሚ አቶ አስመላሽ በቀለ በአገራችን ከሚከበሩ በዓላት ውስጥ የኢሬቻ በዓል የፍቅር፣ የሠላም፣ የወንድማማችነት እና የአብሮነት እሴት ያለው በዓል መሆኑን ገልጸው፣ ማህበረሰቡ በዚህ በዓል ላይ ያሳየውን አንድነት እና ድምቀት በሌሎች ውጭ አገራት ለሚገኙ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ተምሳሌት መሆኑ በመግለፅ በአገራችን እየተከናወኑ ባሉት አገራዊ የልማት ሥራዎች የሚያደርጉትን ተሳትፎ ይበልጥ እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርበዋል::

በመቀጠልም የአቡዳቢ ኤምባሲ ተወካይ አቶ ግርማ ደምሴ የዘንድሮውን ኢሬቻ ልዩ የሚያደርገው ከአገራችን የማንሰራራት ብስራት ጋር አብሮ እየተከበረ በመሆኑ ነው ብለው ለዚህም ማሳያው የዘመናት ቁጭታችን ውጤት የሆነው የሕዳሴ ግድብ ፕሮጄክት መመረቁ፣ የተፈጥሮ ጋዝ ምርት መጀመሩ እና ለአገራችን አርሶ አደሮች ትልቅ ግብዓት የሆነው የማዳበሪያ ፋብሪካ መጀመሩን አንስተዋል::

በተጨማሪም በዱባይ እና ሰሜን ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የሥራ አመራር ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ኢድሪስ ቡንሱሩ የኢሬቻ በዓል በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች በጥቂት ሰዎች ተጀምሮ በየዓመቱ እያደገ መምጣቱን በመጥቀስ ዛሬ በሚታየው ደረጃ ላይ እንዲደርስ አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትን አመስግነው የኮሚኒቲ ማህበሩ በፍቅር፣ በመቻቻል እና በመከባበር መርህ ኅብረተሰቡን በትጋት እያገለገለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በበዓሉ ላይ የኢሬቻ በዓል በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ዲፕሎማቶችና ሠራተኞች፣ የዱባይና አቡዳቢ የኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ ማህበር ሥራ አመራር ቦርድ አባላት፣ የተለያዩ የአገራችን ብሔር ብሔረሰቦች ተወካዮች፣ አባ-ገዳዎች፣ ሃዳ ሲንቄዎች እንዲሁም በርካታ ቁጥር ያለው ዜጎች ታድመዋል፡፡

Unknown's avatar

About advocacy4oromia

The aim of Advocacy for Oromia-A4O is to advocate for the people’s causes to bring about beneficial outcomes in which the people able to resolve to their issues and concerns to control over their lives. Advocacy for Oromia may provide information and advice in order to assist people to take action to resolve their own concerns. It is engaged in promoting and advancing causes of disadvantaged people to ensure that their voice is heard and responded to. The organisation also committed to assist the integration of people with refugee background in the Australian society through the provision of culturally-sensitive services.

Posted on October 24, 2025, in Uncategorized. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a comment