ዳውድ ኢብሳ: አንጋፋ ታጋይ እና የኦነግ መሪ

ትውልዱ ሆሮ ጉዱሩ ሲሆን ከአራት ኪሎ ዩንቨርስቲ በስታትስቲክስ ተመርቋል በተማሪዎች እንቅስቃሴ ወቅት ደርግ ለሁለት አመታት አሰሮ ፈትቶት ነበር ከእስር ሲለቀቅ ወደ ኦነግ የትጥቅ ትግል ገባ ። ኦነግ በ1968 ሃያ ስምንት ማእከላዊ ኮሚቴ ስመረጥ ይህ ሰው አንዱ በመሆን ተመረጠ ፡፡ ወቅቱ 1971 ነው ኦነግ ትግሉን በምእራብ ኢትዮጵያ ለማሰፋፋት ሲወስን ዳውድ ኢብሳ እና የኦቦ ሌንጮ ለታ ወንድም አባ ጫላ ለታ ዋናና ምክትል ሆነው የምእራቡን ትግል እንዲመሩ ተመድበው በጥቅሉ 17 የሰው ሀይል በመያዝ በሱዳን በኩል አቋረጠው ወለጋ ቤጊና ጊዳሚ አከባቢ እንቅሰቃሴ ይጀምራሉ፡፡

ደርግ ይህን የኦነግ የምእራብ እንቅስቃሴ ለማፈን ትኩረት ሰጥቶ ማጥናት ይጀምራል፡፡ በወቅቱ የጊዳሚ ወረዳ አሰተዳዳሪ ሂካ መሳዲ እና የወለጋ ክ/ሀገር አሰተዳዳሪ ንጉሴ ፋንታ የኦነግን የትግል ጅማሮ ለማጨናገፍ አንድ መላ ይዘይዳሉ፡፡ በጃሌ ዳውድ ኢብሳ ይመሩ ከነበሩት 16 ታጋዮች የአንዱ ወንድም ዘካሪያስ ሾሮ ይባላል፡፡

.የጊዳሚ ወረዳ አስተዳዳሪ ደነበረው ሂካ መሳዲ ዘካርያስን ጠርቶ እንዲህ የሚል ግዳጅ ይሰጠዋል። ወንድምህንና ጓደኞቹን ቤትህ እራት ትጋብዛቸዋለህ የምንሰጥህን መርዝ ደግሞ ምግቡ ውስጥ ትጨምርና ታበላቸዋለህ፡፡ ይህን የማትፈጽም ከሆነ ከእነ ቤተሰብህ ትገደላለህ! ከብትህ ይዘረፋል! መሬትህን ታጣለህ! ዘርህ ከምድረ ገጽ ይጠፋል…..”
.
ዘካሪያስ ግዴታ ሆኖበት እንደ ተሰማማ የደህንነቱ ሪፖርት ላይ ተጠቅሷል፡፡” ወንድሜንስ እንዴት ብዬ እገላለው…” ብሎ አቅማምቶ ነበር፡፡ የተሰጠው ምላሽም “….እንግዲያውስ ከቻልክ ወንድምህን ለይተህ እንዳይበላ አድርገው፡፡ ካልተቻለ ግን አብሮ ይሙት! ወንድምህ አገር ሊያጠፋ የተቀጠረ ከሃዲ ነው” በማለት በግልጽ ይነግሩታ፡፡

..ይህ ዝግጅት ከተደረገ ቦሀላ የገበሬ ልብስ የለበሱ ወታደሮች በአከባቢው አድፈጠው ዘካርያስ ሾሮ እንዳያመልጥ ይጠብቁት ነበር፡፡ ምግብ ውሰጥ የሚጨመር መረዝ ከአዲሰ አበባ ተልኮ በንጉሴ ፋንታ በኩል ለሂካ መሳዲ ተሰጠ፡፡ሂካ መሳዲ ለዘካርያስ አሰረከበው፡፡

…በንጉሴ ፋንታ ትእዛዝ የተገዛው ሙክት ከተላከ ቦሀላ ዘካርያስ ለወንድሙና ለጓደኞቹ የራት ግብዣ ጥሪ እንዲላክላቸው ተደረገ፡፡ ቀጥሎም በጉ ታርዶ ጥሩ ምግብ አዘጋጀ፡፡ በዚያን ሰሞን 17ቱየኦነግ ታጋዮች ለሁለት ተከፍለው ነበር የሚንቀሳቀሱት፡፡ አባ ጫላ ዘጠኝ ራሱን ሆኖ በሌላ አቅጣጫ ይንቀሳቀሰ ነበር፡፡ ዳውድ ኢብሳ የሚመራት ቲም የዘካርያስን የራት ግብዣ ተቀብለው ማምሻው ላይ በገበታው ዙሪያ ተገኙ፡፡

በሰአቱም ዘካርያስ ወንድሙን ለይቶ ለማሰቀረት ሳይቻለው ቀረ፡፡ “…አንተ ቆይ ቦሃላ ትበላለህ ..”ቢለውም ወንድሙ አሻፈረኝ ብሎ ለገበታው ቀረበ፡፡ ወንድሙና ጓደኞቹ በመረዝ የተለውሰውን ምግብ ሲበሉ ዘካርያስ የጎጆውን ምሰሶ ተደግፎ በትካዜ እና በሰቆቃ ይመለከታቸው ነበር፡፡
ዳውድ ኢብሳ ከምግቡ ትንሽ ቀማምሶ ደጅ ጥበቃ ላይ የነበረው ጓደኛቸውን ለመተካት ገበታውን ትቶ ወደ ደጅ ወጣ፡፡ ሌሎች የተመረዘውን ምግብ መብላቱን ቀጠሉ ነገር ግን ብዙም ሳይቆዩ መላ ሰውነታቸው እንደ እሳት እያቃጠላቸው እየጮሁ ይወድቁ ጀመረ፡፡

ዘካርያስ የታናሽ ወንድሙን ሬሳ እጁ ላይ ታቀፈ፡፡ ዳውድ በወቅቱ ብዙም የተመገበ ባይሆንም ከመመረዝ አላመለጠም፡፡ በጥበቃው ላይ እያለ ሰውነቱ ሲቃጠልበት መመረዛቸው ስለገባው በፍጥነት ቅጠላ ቅጠልና አፈር እየቃመ ውሃ በብዛት ጠጣበት፡፡ ደግሞ ደጋግሞ አሰታወከ፡፡ሆኖም ከመውደቅ አልዳነም፡፡ራሱን ስቶ እንደ ጓደኞቹ ከዘካርያስ ጓሮ ወደቀ፡፡ የገበሬ ልብስ ለብሰው በአከባቢው አድፍጠው ውጤቱን ይጠብቁ የነበሩ ወታደሮች በተያዘላቸው ቀጠሮ ዘካርያስ ቤት ሲደረሱ ሰባቱ ታጋዮች ሞተው ዳውድ ኢብሳ ግን ነፍሱን እንደሳተ አገኙት፡፡

ዳውድነን ይዘው ወደ ደምቢዶሎ ከነፉ፡፡ የኦነግን ሚስጥር ከእሱ ለማግኘት ፍላጎት ሰለ ነበራቸው ፈጣን ህክምና ሰጥተው ህይውቱን አተረፉት፡፡ ቀጥሎም ከደምቢ ዶሎ ወደ ነቀምት አዘዋውረውት ተጨማሪ ህክምና ሰጡት፡፡
ነቀምት ላይ ትንሽእንዳገገመ ወደ እስር ቤት በመውሰድ ገልብጠው ይገርፉት ጀመር፡፡ በወቅቱ ስለ ሁኔታው የተገኘው ማስረጃ የወለጋው የደህንነት ሪፖርት እንደሚገልጸው አሉ የተባሉትን የምርመራ እርምጃዎችን
የተጠቀሙበት ቢሆንም ከዳውድ ኢብሳ አንደበት አንዳችም ሚሰጢር ሊያገኙ አልቻሉም፡፡ሲያቅታቸው ወደ አዲሰ አበባ ወደ ማእከላዊ ላኩት፡፡

እዚያም በቤንዚንና በቆሻሻ ውሃ የሞላ በርሜል ውሰጥ እየደፈቁ መረመሩት፡፡ ለመሞት ዝግጁ ሰለ ነበር አንዳችም የተነፈሰው ነገር የለም፡፡ደግመው ደጋግመው ማእከላዊና አለም በቃኝ እያመላለሱ በተለያዪ ማሰቃያ ሰልቶች እንደ መረመሩት የደህንነቱ መ/ቤት ሰነድ በዝርዝር ያብራራል፡፡
ዳውድ ኢብሳ! በአለም በቃኝ አምስት አመታት ታሰረ፡፡ በሂደትም ከመላመድ ብዛት ጠባቂ የነበረውን ፖሊስ ማሳመን ቻለ። ለህክምና ሲወጡም ከሁለት ባልደረቦቹ ጋር ከሆስፒታል አምልጦ ወለጋ ገባ፡፡
.
የቤንሻጉል ጫካዎችን በማቋረጥ ዳግም ኦነግ ከአለበት ቦታ ለመድረሰ የሁለት ሳምንት የሌሊት ጉዞ አድርጓል፡፡ እሱ መርዝ በልቶ ሲማረክ ምእራብ ወለጋ ጫካ ውሰጥ የቀሩት አባጫላ ለታ እና ዘጠኝ ጓደኞቹ ከአንድ ብርጌድ በላይ ሰራዊት ሆነው ነበር የጠበቁት፡፡ የመሪያቸውን በህወይት መመለስ ማመን ያልቻሉት ታጋዮች በታላቅ ደሰታ ተቀበሉት!!
.
ይህ ተአምር ከሞት_የተረፈ_በብልጠቱ_ከደርግ_እስር_ቤት ያመለጠው ሰው የዛሬው_ የኦነግ_ ሊቀመንበር_ ጃሌ_ ዳውድ_ኢብሳ_ነው ፡፡ ዳውድ ኢብሳ ባመነበት የትግል መንገድ ለኦሮሞ ህዝብ ህልውና ሲል ሲታገል እና ሲያታግል እድሜው የጨረሰ ጀግና ነው ። ታሪክ ታሪክ ነው እና የምናውቀውን አጋራናችሁ ።

Advertisement

About advocacy4oromia

The aim of Advocacy for Oromia-A4O is to advocate for the people’s causes to bring about beneficial outcomes in which the people able to resolve to their issues and concerns to control over their lives. Advocacy for Oromia may provide information and advice in order to assist people to take action to resolve their own concerns. It is engaged in promoting and advancing causes of disadvantaged people to ensure that their voice is heard and responded to. The organisation also committed to assist the integration of people with refugee background in the Australian society through the provision of culturally-sensitive services.

Posted on May 11, 2020, in Events, Finfinne, News, Oromia. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: